ያወረዱትን ያረጋግጡ

የKazaVPN Linux ልቀቶች የተፈረሙ ናቸው። የልቀቱን ፊርማ ለማረጋገጥ እና ያወረዱትን ጥቅል ከታተመው አሻራው ጋር ለማነጻጸር ከታች ያሉትን ሁለት ትዕዛዞች ይጠቀሙ።

በማውረጃ ገጹ ይጀምሩ

ለኮምፒውተርዎ የሚሆነውን ጥቅል ከዚያ ይውሰዱ። ያ ልቀት ያተመው የአሻራዎች ፋይል፣ ፊርማው እና የልቀት ቁልፋችንም ያስፈልግዎታል። ፋይሎቹን ከማረጋገጥዎ በፊት የልቀት ቁልፋችንን ከዚህ መመሪያ ያውርዱ።

የልቀት ቁልፉን ያግኙ

የአሻራዎች ፋይሉን እና ፊርማውን በዚያው ልቀት ውስጥ ከጥቅሉ ጎን ያገኛሉ።

ፊርማውን፣ ከዚያ ፋይሉን ያረጋግጡ

ሁለቱንም ትዕዛዞች ፋይሎቹን ባወረዱበት አቃፊ ውስጥ ያሂዱ። የመጀመሪያው የአሻራዎች ፋይሉን ከዚህ መመሪያ ካወረዱት የልቀት ቁልፍ ጋር ያረጋግጣል። ሁለተኛው ጥቅልዎን ከዚያ የአሻራዎች ፋይል ጋር ያነጻጽራል፣ ከተመሳሰለም ስሙን ከOK ጋር ያሳያል።

ጥቅሉን ከመጫንዎ በፊት ሁለቱም ማረጋገጫዎች ማለፍ አለባቸው። የሚመሳሰል አሻራ ብቻውን ዝርዝሩን ማን እንዳተመው አያረጋግጥም። ትክክለኛ ፊርማ ብቻውን ጥቅልዎ ከዝርዝሩ ጋር እንደሚመሳሰል አያሳይም።

ssh-keygen -Y verify -f kazavpn-release.pub -I release@kazavpn.com \
  -n kazavpn-release -s SHA256SUMS.sig < SHA256SUMS
sha256sum --ignore-missing -c SHA256SUMS

ይጫኑት

በማውረጃ አቃፊው ውስጥ ሊጭኗቸው የሚፈልጓቸውን የKazaVPN ጥቅሎች ብቻ ያስቀምጡ: ለኮምፒውተርዎ የሚሆኑትን የዴስክቶፕ መተግበሪያ እና የትዕዛዝ መስመር። ሁለቱንም ከሚያስፈልጓቸው ጋር ለመጫን ለሲስተምዎ የሚስማማውን ከታች ያለውን ትዕዛዝ ያሂዱ። ከዚያ ይግቡ፣ ቦታ ይምረጡ እና ይገናኙ።

.deb

sudo apt install ./kaza*_$(dpkg --print-architecture).deb

.rpm

sudo dnf install ./kaza-*.rpm ./kazavpn-*.rpm

አንድ ማረጋገጫ ካላለፈ

ፋይሉን አይጫኑ። እንደገና ያውርዱት፣ ሌላ አውታረ መረብ ካለዎት በእሱ ላይ፣ እና ሁለቱንም ትዕዛዞች አንድ ጊዜ ደግመው ያሂዱ። ለሁለተኛ ጊዜ ካልተሳካ፣ ሌላ ነገር ከማድረግዎ በፊት ይጻፉልን፣ ከሁለቱ የትኛው እንዳልተሳካም ይንገሩን።

ከቡድናችን እገዛ ያግኙ

የKazaVPN Premium እና የKazaVPN Family አባላት ከቡድናችን ከአንድ ሰው በኢሜይል መልስ ያገኛሉ።

ባሉዎት መሣሪያዎች ሁሉ ላይ አንድ መለያ